
03/07/2025
የተነቃቃ የባለሙያዎች ንቃተ ሂሊና ለዕቅድ አፈጻጸም ስኬቶች ጉልህ ሚና አለው፤
#ዲላ ሰኔ 26/2017 ዓ.ም (ጌዞባቱ)
በበጀት ዓመቱ መጨረሻ በዲላ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት የታክሲ ህግ ማስከበር ዋና የሥራ ሂደት በተግባር አፈጻጸም ላይ የቆዩት ባለሙያዎች የጌዴአ ዞንን ታሪካዊ የቱቲቲ እና ቱቶፈላ መካነቅርስ ስፍራዎችን ጉብኝት አድርገዋል።
በዲላ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት የታክሲ ህግ ማስከበር ዳይረክቶሬት ዳይረክተር ወ/ሮ አዶናይት ጥላሁን እንደተናገሩት በዞናችን በዩኔስኮ የተመዘገቡ ባህላዊ መልካዓምድር ውስጥ የተደበቁ በርካታ የቱሪስት መዳረሻዎች የቱሪዝም ዕምቅ ሃብቶቻችን ዓለም ዓቀፋዊ ትኩረት በማግኘት ከሀገር ውጪ እና ከሌሎች የሀገራችን የጉብኝት ማዕከላት እየሆኑ መጥተዋል።
እንደ ዞናችን የጉብኝት ባህላችንን በማዳበር የዞኑን የቱሪስት መዳረሻዎች አውቆ ከማስተዋወቅና መረጃዎችን ከማዳረስ አንጻር በሁሉም ተቋማት የጉብኝቱ ባህል መዳበር እንዳለበት ገልጸዋል።
አክሎም ይህ የስራ ሂደት በዲላ ከተማ ውስጥ ከታክስ ህግ ማስከበር ሥራ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የስራ ውጥረት የምታይበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በዓመቱ የሴክተሩን ዕቅድ ከግብ በማድረስ የተሻለ አፈጻጸም እንድናስመዘግብ ባለሙያዎቻችን በእጅጉ ተግተዋል ብለዋል።
በበጀት ዓመቱ በስራ ሂደቱ የሥራ አፈጻጸም ስተጉ የቆዩ ባለሙያዎች ለቀጣይ የስራ ዘመን ዕቅዱን በተነቃቃ አዕምሮ ተግባራትን ለመፈጸም ዝግጁ በመሆን ንቃተ ህሊናቸውን እንድያድሱ ታስቦ የተደረገ የዞኑ የቱሪስት መስህቦች ጉብኝት ጉዞ እንደሆነ አስረድተዋል።
በጉብኝቱ የተሳተፉ አጠቃላይ የዳይረክቶሬቱ ባለሙያዎች በተመለከቱ መስህቦች ታሪካዊነት እና ከዞኑ የቱሪዝም ፕሮሞሽን ባለሙያ በኩል ባገኙት ብርቱ ገለጻ ባገኙት ግንዛቤ መደሰታቸውን መናገራቸውን የገለጸው፦
የጌዴኦ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ቱሪዝም ፕሮሞሽን ነው።