Undiscovered Ethiopia Tours

Undiscovered Ethiopia Tours Book Now for family, group, or individual tour needs in Ethiopia 🇪🇹 We offer professional and enriching experience throughout your journey.

ሰላም ለናንተ ይሁን    ዘውትር ቅዳሜ በአባይ ቴሌቪዥን ምሽት አንድ ሠአት ይጠብቁን🙏         አብረን እንጓዛለን ......        ድንቅነሽ አፍሪካ        ከ ሰያ ጋር
14/05/2024

ሰላም ለናንተ ይሁን
ዘውትር ቅዳሜ በአባይ ቴሌቪዥን ምሽት አንድ ሠአት ይጠብቁን🙏
አብረን እንጓዛለን ......
ድንቅነሽ አፍሪካ
ከ ሰያ ጋር

✨ድንቅነሽ አፍሪካ
💫በልዩ ሁኔታ ከሀገራችን ታሪክ እስከ አህጉራችን አፍሪካ ባህል፣ወግ፣ታሪክ ሁሉንም አሰናድተን በዓባይ ቲቪ መተናል
⚡️ግንቦት 10 በዓባይ ቲቪ ይጀምራል!!!

13/03/2024

አክሱም የአፍሪካ የታሪክ ማማ #አክሱም #ትግራይ #ኢትዮጵያ #ሀበሻ

ዱባይ የመሰለችዋን ስንት የለፋሁባት ወንጪን ልጋብዛቹ       ግቡ subscribe አድርጉኝ ቤተሰብም ሁኑኝ     ሊንኩን Comment መስጫው ላይ አስቀምጫለሁ🙏                  ...
08/01/2024

ዱባይ የመሰለችዋን ስንት የለፋሁባት ወንጪን ልጋብዛቹ
ግቡ subscribe አድርጉኝ ቤተሰብም ሁኑኝ
ሊንኩን Comment መስጫው ላይ አስቀምጫለሁ🙏
አመሰግናለሁ🙏

#ጉዞ
#ኢትዮጵያ #ሰላም #ሀበሻ Ethiopia

ሰላም ለናንተ ይሁን     የሶስት ቀንና የሁለት ምሽቶች ጉዞ ወደ ጥበብ ምድር ውቢቷ አርባምንጭ💚💚💚🐊       ከሰኔ 30 እስከ ሀምሌ 2 አርብ ቅዳሜ እሁድ     ከውቡ ነጭ ሳር አርባዎቹ ...
03/07/2023

ሰላም ለናንተ ይሁን
የሶስት ቀንና የሁለት ምሽቶች ጉዞ ወደ ጥበብ ምድር ውቢቷ አርባምንጭ💚💚💚🐊
ከሰኔ 30 እስከ ሀምሌ 2 አርብ ቅዳሜ እሁድ
ከውቡ ነጭ ሳር አርባዎቹ ምንጭ እስከ አዞ ገበያ ዶርዜ መንደር ሃዋሣን የምንጎበኝበት ልዩ ጉዞ ይሆናል።
ከማይረሱ ጨዋታና 😁🥰😍💚ትዝታዎች ጋር በተለይም እጅግ ውብ 💚🐊በሆነበት በአሁን ሰአት የማይረሳ ጊዜን ማሳለፍ ከፈለጉ በጊዜ ቦታዎትን ይያዙ።
ለተጨማሪ መረጃ ለመመዝገብ 0938177562
LETS DISCOVER ARBAMINCH🏡🐊 from July 9-11
Time To Visit Beautiful Arbaminch plus DORZE village 💃🕺
THINGS TO DO
👉🏾Visit Nechasar National Park💚💚💚
👉🏾Swimming on natural swimming pool 🏊🏼‍♀️
👉🏾Visit DORZE village and experience there day to day life. 🥁🪘
👉🏾Boat Trip On Lake Chamo 🚢
👉🏾Visit Crocodile market 🐊🌅
👉🏾Campfire 🔥🔥
👉🏾Games and so on…..🌅🌅
Book your Sit now!
For booking or extra information call us ☎️ 0938177562
Thank you 🙏

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ እህት ወንድሞች በሙሉ፣ እንኩዋን ለታላቁ አረፉ በአል በሰላም አደረሳችሁ።      በዱአቹ ሀገራችንን አትርሱ!🤲🤲    የደስታ የፍቅር በአል እንዲሆንላችሁ ...
08/07/2022

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ እህት ወንድሞች በሙሉ፣ እንኩዋን ለታላቁ አረፉ በአል በሰላም አደረሳችሁ።
በዱአቹ ሀገራችንን አትርሱ!🤲🤲
የደስታ የፍቅር በአል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!

For All Muslim Brothers And Sister's Wishing You A Happy EIDEL ADEHA AREFA Celebration!
Wishing You A Wonderful Holliday!

🤲🤲🤲🤲
ETHIOPIA 🇪🇹

ሰላም ለናንተ በያላችሁበት ሁሉ ይሁን                  ሀረር          ክፍል1ከ አዲስ አበባ ደቡብ ምስራቅ በአምስት መቶ ሃያ አምስት ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ የምስራቅ ፈ...
15/05/2022

ሰላም ለናንተ በያላችሁበት ሁሉ ይሁን
ሀረር
ክፍል1
ከ አዲስ አበባ ደቡብ ምስራቅ በአምስት መቶ ሃያ አምስት ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ የምስራቅ ፈርጥ ሐረር ከተማ። በዘመኑ የአስተዳደር መዋቅር የሃረሪ ክልል ዋና ከተማ ናት። በ1,885 ሜትር ከፍታ ላይ፣ የወይና ደጋ የአይር ጠባይ በተላበሰ ቦታ ላይ አርፋለች።

ሐረር ለዘመናት ከፍተኛ የንግድ ማዕከል ሆና ስትኖር ከመሃል አገር፣ ከ አፍሪካ ቀንድ እና ከአረብ አገራት ጋር በንግድ መንገዶች ስትገናኝ ከቀሪው አለም ጋር ደግሞ በቀይ ባህር ወደቦች አማካኝነት ትገናኝ ነበር።

የሐረር ጀጎል ግንብ ከ1998 ጀምሮ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ዝርዝር ውስጥ ይገኛል። በእስልምና ሃይማኖት "4ኛዋ የተቀደሰች ቦታ" እየተባለች በብዙ የውጭ ፃሀፍቲያን የሚነገርላት ሀረር ከ90 በላይ መስጊዶች፤ አንዳንዶቹ ከ10ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የነበሩ፤ እንዲሁም 102 የቀብር ቦታዎች አሉዋት።

አባዲር (ሼህ ዑመር አርሪዳ) (በግምት ወደ ፲፫ ኛው ክ/ዘ)፦ በ ፲፫ ኛው ክ/ዘመን ውስጥ የተፃፈውና ስለ ሐረር ጥንታዊ አፈታሪካዊ ታሪክ የሚዘክረው 'ፋዝ መዲናት ሐረር' የተባለው ያልታተመ መጽሐፍ እንደሚገልጸው አባድር (ሼህ ዑመር አርሪዳ) እጅግ ከተከበሩት የሐረር ሼኽዎች ውስጥ አንዱና ዋንኛው ናቸው። በዚሁ መጽሓፍ አገላለጽ መሠረት፡ አባድር ከሌሎች በርካታ ሼኾች ጋር በመሆን ከሂጃዝ በ፮፻፩፪ ሂጅሪያ (1216 እ.ኤ.አ) ተነስተው ሐረር ከገቡ በኋላ በአካባቢው የጎሣ እና ኃይማኖት መሪዎች ተመርጠው ዒማም ሆኑ። የሀረር ህዝብ ታሪክ ፣ ባህል እና ማንነት ከሀረር ከተማ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው፡፡ ሀረሪዎች በረዥም ዘመን የስልጣኔ ታሪካቸው ያፈሯቸው ተንቀሳቃሽ እና የማይንቀሳቀሱ እንዲሁም የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ በርካታ ቁሳዊ እና መንፈሳዊ ቅርሶች ባለቤት ናቸው፡፡ ከእነዚህ ቅርሶች መካከልም የከተማዋ ልዩ መለያ ምልክት ከመሆንም አልፎ እ.ኤ.አ በ2006 በአለም ቅርስነት የተመዘገበው የጀጎል ግንብ በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡በግንቡ ውስጥም ከ90 በላይ መስኪዶች እና ከ2000 በላይ የሀረሪ ባህላዊ ቤቶች ይገኛሉ፡፡

ሀረር ከፍተኛ የስልጣኔ እድገት ደረጃ ላይ በደረሰችበት በ16ኛው ክፍለ ዘመንም በምስራቅ አፍሪካ የእስልምና ሀይማኖት ትምህርት እና የንግድ ማዕከል ሆናም አገልግላለች፡፡ ይህም የበርካታ ታሪካዊ እና ባህላዊ ቅርሶች ባለቤት እንድትሆን አድርጓታል፡፡ የጀጎል ግንብ የሀረሪ ህዝብ የኪነ ህንፃ ችሎታውን የሚያስመሰክር የታሪክ እና የጥበብ መዘክር ነው፡፡ ይህ ግንብ በ16ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ በአሚር ኑር አማካኝነት እንደተገነባም ይነገራል፡፡ሐረር እንኳን ዛሬ ቀን ዘምኖ ትናንትናም ቢሆን ስንቱ ባህር አቋርጦ የከተመባት፤ ስንቱ ቅጥሯ ገብቶ ለትውልድ የተረፈ ትዝታ ያስቀመጠባት የውበትና የጥበብ መዲና ናት፡፡ የኢትዮጵያ ኢስላማዊ ኪነ ህንጻና ባህል ማንምም ሳይመስል፤ ሃይማኖታዊ መሰረቱን ሳይጥል የነገሰባት መዲና፤ ያው ጀጉልን መዞር ነው፡፡ በየቦታው መቆም፡፡ በየቦታው ማየት….በየቦታው መደምም…ጀጉልን ገብተው ይኖሯታል እንጂ አይጽፏትም.........

የኔ ቤተሰቦች በያላቹበት ሁሉ ሰላማቹ ይብዛ።     ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ቤተሰቦቼ በሙሉ እንኩዋን ለትንሳኤ በአል በሰላም አደረሳቹ።    መልካም በአል በያላቹበት ሁሉ እንዲሆን...
24/04/2022

የኔ ቤተሰቦች በያላቹበት ሁሉ ሰላማቹ ይብዛ።
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ቤተሰቦቼ በሙሉ እንኩዋን ለትንሳኤ በአል በሰላም አደረሳቹ።
መልካም በአል በያላቹበት ሁሉ እንዲሆንላቹ እመኛለው።
አመሠግናለሁ!

Address

Harer

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Undiscovered Ethiopia Tours posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category