Amhara wollo Kombolicha tourist information center

Amhara wollo Kombolicha tourist information center የኮቦልቻ አየርመገድ የቱሪስት መረጃ መስጫ ማዕከል

21/05/2026

ጣና ቂርቆስ

በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ቀደምት ሀይማኖታዊ ቦታዎች መካከል አንዱ የጣና ቂርቆስ ገዳም ነው፡፡ ከኦሪት እስከ ክርስትና የረጅም ዓመት ታሪክ ባለቤት የሆነው ጣና ቂርቆስ ገዳም የሚገኘው በደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ አስተዳደር ከጣና ሐይቅ ምስራቅ ዳርቻ ነው፡፡ ገዳሙ ክረምት ሙሉ በሙሉ በሐይቁ የሚከበብ ሲሆን በበጋ ወቅት ከየብስ ጋር የሚገናኝበት ማራኪ ቀጭን ተፈጥሯዊ መንገድ አለው፡፡

የጣና ቂርቆስ ገዳም ከ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በፊት የኦሪት መስዋዕት የቀረበበት፣ ታቦተ ጽዮን ለረጅም ዓመታት ያረፈችበት፣ ቅድስት ድንግል ማርያም በስደት ለ13 ወራት የቆየችበት፣ ቅዱስ ያሬድ የዜማ እና ድጓ መጻሕፍቱን የደረሰበት፣ የኢትዮጵያን ውድ ቅርሶችን ለማከማቻ የተመረጠ እንዲሁም ከአራቱ የኢትዮጵያ መናብርት አንዱ የነበረ ድንቅ ሀይማኖታዊ መዳረሻ ነው፡፡

ከባህር ዳር ከተማ የሦስት ሰዓት የጀልባ ጉዞ ርቀት ላይ በሚገኘው ጣና ቂርቆስ ከጥንታዊው የጣና ቂርቆስ ገዳም በተጨማሪ ደምበዛ ቁስቋም፣ ቅዱስ ያሬድ እና ፅዮን ማርያም የሚባሉ ሌሎች አብያተ ክርስቲያናትም ይገኛሉ፡፡ ጥንታዊውን የኢትዮጵያ ታሪክና ቅርስ ለመረዳት፣ ለሀይማኖታዊ ጉዞ እንዲሁም ማራኪውን የጣና ሐይቅ ምስራቃዊ ዳርቻ ለመመልከት ተመራጭ የሆነውን የጣና ቂርቆስ ገዳም ትጎበኙ ዘንድ ግብዣችን ነው፡፡

02/05/2026

የቱሪስት ማዕከሉ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች የቱሪስት መዳረሻዎችን ማስጎብኘትስለመዳረሸዎች በቂ መረጃ መስጠት የአየር ትኬት መቁረጥ የመኪና ኪራይ አገልግሎት መስጠት.የደሊቨሪ አገልግሎት መስጠትለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0933046025 /0710990900 ይደውሉ።

እንኳን ለብርሐነ ትንሳኤ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!
11/04/2026

እንኳን ለብርሐነ ትንሳኤ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!

03/04/2026

Address

Northeast Amhara Region
Kembolcha
25+933046025

Telephone

+251966445820

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara wollo Kombolicha tourist information center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Amhara wollo Kombolicha tourist information center:

Share

Category