Travel Ethiopia tips

Travel Ethiopia tips Ethiopia the roof of African, land of historical wonder

Surprise Lalibela Tours This portrait captures a warm, spontaneous moment: the man’s broad smile immediately draws atten...
19/03/2025

Surprise Lalibela Tours
This portrait captures a warm, spontaneous moment: the man’s broad smile immediately draws attention, radiating a sense of contentment. He wears multiple strands of colorful beads around his neck—red and amber tones that stand out against the neutral background—and a feather adorns the small headband on his forehead. Subtle details, like the gold-toned earrings and the carefully layered necklaces, suggest personal style and cultural identity. His weathered skin and relaxed demeanor evoke a life lived close to the land. Though the background is softly blurred, the earthy tones suggest an open, rural setting—perhaps a village or pastoral landscape. Altogether, the photograph conveys both vibrancy and tranquility, hinting at the richness of his story and the traditions he carries with him.

Lalibela now 📸የቅዱስ ላሊበላ ገፅዎች Face of St.Lalibela
07/11/2024

Lalibela now 📸
የቅዱስ ላሊበላ ገፅዎች Face of St.Lalibela

12/09/2024

መጥሙቁ ቅዱስ ዮሐንስ አመታዊ በአል

መልካም ቀን 📸✅🫡የቅዱስ ላሊበላ ገፅዎች Face of St.Lalibela
01/09/2024

መልካም ቀን 📸✅🫡የቅዱስ ላሊበላ ገፅዎች Face of St.Lalibela

የ2017ዓ.ም የአጽዋማትና የበዓላት ማውጫ ስሌት ‼️🔴👉 5500+2017= 7517 ይህ ዓመቱ ዓለም ይባላል።🔷👉 የ2017 ዓ/ም ወንጌላዊውን ለማወቅ :- ዓመተ ዓለሙን (7517) ለ4ቱ ወንጌ...
29/08/2024

የ2017ዓ.ም የአጽዋማትና የበዓላት ማውጫ ስሌት ‼️

🔴👉 5500+2017= 7517 ይህ ዓመቱ ዓለም ይባላል።

🔷👉 የ2017 ዓ/ም ወንጌላዊውን ለማወቅ :-
ዓመተ ዓለሙን (7517) ለ4ቱ ወንጌላውያን በማከፈል
7517፥ 4=1879 ደርሷቸው 1 ይቀራል።
ይህ ማለት 7517 - 4 × 1879 = 1 ይሆናል።
1879 መጠነ ራብዒት ይባላል።

🔴👉 ልብ በሉ ቀሪው 1 ከሆነ ዘመኑ ማቴዎስ፣ 2 ከሆነ ሉቃስ፣ 3 ከሆነ ማርቆስ ፣ ያለምንም ቀሪ ከተካፈለ ዘመኑ ዮሐንስ ይሆናል ማለት ነው። ስለዚህ በ2017 ዓ/ም ቀሪው 1 ስለሆነ ወንጌላዊው ማቴዎስ ይሆናል ማለት ነው።

🔷👉 የመስከረም መባቻ የሚውልበትን ዕለት ለማወቅ፦

👉 ዓመተ ዓለም ሲደመር መጠነ ራብዒት
7517+1879= 9396 ይህ ለ7ቱ ዕለታት ሲካፈል
9396 ፥ 7 = 1342 ደርሶ ቀሪው 2 ነው።
ይህ ማለት 9396 - 7 × 1342 = 2 ይሆናል።

🔴👉 ልብ በሉ ሲካፈል ያለምንም ቀሪ በዜሮ ከተካፈለ ቅዱስ ዮሐንስ ሰኞ ዕለት ይውላል፣ ቀሪው1 ከሆነ ማክሰኞ ፣ 2 ከሆነ ረቡዕ ፣ 3 ከሆነ ሐሙስ ፣ 4 ከሆነ ዓርብ ፣ 5 ከሆነ ቅዳሜ ፣ 6 ከሆነ እሑድ ቀን ይውላል።

🔷👉 ስለዚህ የ2017 ዓ/ም ቀሪው 2 ስለሆነ የመስከረም መባቻ ረቡዕ ዕለት ይውላል ማለት ነው።

🔴👉 የዘመኑን ወንበር ለማግኘት፦

👉 ዓመተ ዓለሙን ለንዑስ ቀመሩ ማካፈል
7517፥19 =395 ደርሶ 12 ይተርፋል።
1 ለዘመን ትተን 11 ይቀራል።
🔷👉 ስለዚህ የ2017 ዓ/ም ወንበሩ 11 ይሆናል ማለት ነው።

🔴👉 የዘመኑን አበቅቴን ለማወቅ ፦

👉 365 -354= 11ይህ ጥንተ አበቅቴ ይባላል።
ስለዚህ አበቅቴን ለማወቅ ፣ የዘመኑ ወንበር ሲባዛ
11x11=121 በአራት 30 ስንገድፍ 1 ይቀራል።

🔷👉 ስለዚህ የ2017 ዓ/ም አበቅቴ 1 ይሆናል ማለት ነው።

🔴👉 መጥቅዕን ለማወቅ ፦

👉 መጥቅዕን ለማግኘት ወንበሩን በንዑስ ቀመር አባዝቶ በ30 ገድፎ የሚገኘው ነው።
11x19 = 209 በ6 ሠላሳ ሲገደፍ 29 ይቀራል።

🔴👉 ልብ በሉ መጥቅዕ ከ14 በላይ ከሆነ በመስከረም ፣ ከ14 በታች ከሆነ በጥቅምት ወር ላይ ይውላል። 14 ራሱ መጥቅዕ አይሆንም።

🔷👉 ስለዚህ የ2017 ዓ/ም መጥቅዕ 29 ይሆናል ማለት ነው።
እናም የ2017 ዓ/ም ከ14 በላይ 29 ስለሆነ በመስከረም ይውላል።

🔴👉 ልብ በሉ አበቅቴና መጥቅዕ ተደምሮ ከ30 አይበልጡም ፣ከ30 አያንሱም ሁልጊዜ 30 ይሆናሉ እንጂ።

🔴👉 ተውሳክ፦

👉 ተውሳክ ማለት፦ ጭማሬ ማለት ነው። እሱም በዓላቱንና አጽዋማቱን ለማወቅ ከመጥቅዕ ጋር እየተጨመረ የሚቆጠር ነውና። 3 ዓይነት ተውሳኮች አሉ። እነሱም ፦ የዕለታት ፣ የበዓላት እና የአጽዋማት ተውሳኮች ናቸው።

🔴👉 የዕለታት ተውሳኮችን ለማግኘት መጥቅዕ ከዋለበት ሳኒታ(ማግሥት) ጀምረን ነነዌ እስከ ዋለችበት ቀን ስንቆጥር ከ122-128 ቀናት ናቸው የሚሆኑት።

🔷👉 ከመጥቅዕ ማግሥት ነነዌ እስከ ዋለችበት ቀን እየቆጠሩ 125ቱን በ30 እየገደፉ ቀሪውን በመያዝ የዕለት ተውሳክ ይገኛል።
መጥቅዕ ከዕለታት ተውሳክ ጋር ተደምሮ ጾመ ነነዌን ያስገኛል።

የዕለት ተውሳክ በቅዳሜ ይጀምራል።
1. የቅዳሜ ተውሳክ 8 ነው
2. የእሑድ ተውሳክ 7 ነው።
3. የሰኞ ተውሳክ 6 ነው።
4. የማክሰኞ ተውሳክ 5 ነው።
5. የረቡዕ ተውሳክ 4 ነው።
6. የሐሙስ ተውሳክ 3 ነው።
7. የዓርብ ተውሳክ 2 ነው።

🔷👉 ስለዚህ የ2017 ዓ/ም የነነዌ ጾም መቼ እንደሚገባ ለማወቅ ከዚህ በታች ያለውን ፎርሙላ ይመልከቱ።

👉 በ2017 ዓ/ም መጥቅዕ የዋለው መስከረም 29 ቀን ነው። መስከረም 29 የሚውልበት ዕለት ረቡዕ ነው። የረቡዕ ተውሳክ 4 ነው። ስለሆነም 29+4=33 በአንድ 30 ሲገደፍ 3 ይቀራል።

🔷👉 ስለዚህ በ2017 ዓ/ም ጾመ ነነዌ የካቲት 3 ቀን ትገባለች ማለት ነው። እሷም > ትባላለች። ከዚህ በኋላ መባጃ ሐመሩን ወይም የነነዌ የገባችበትን ቀን ከአጽዋማቱና በዓላቱ ጋር እየደመሩ ከ30 ያለፈውን በ30 እየገደፉ ቀሪውን የበዓሉን ወይም የአጽዋማቱን መግቢያ ማግኘት ይቻላል።

1. የዐቢይ ጾም ተውሳክ 14 ነው። 14+3=17 ስለዚህ ዐቢይ ጾም የካቲት 17 ይገባል ማለት ነው።
2. የደብረ ዘይት ተውሳክ 11 ነው። 11+3=14 ። ስለዚህ መጋቢት 14 ደብረ ዘይት ይሆናል ማለት ነው።
3. የሆሣዕና ተውሳክ 2ነው ። 2+3=5።
ስለዚህ ሚያዝያ 5 ሆሣዕና ይሆናል ማለት ነው።
4. የስቅለት ተውሳክ 7 ነው። 7+3=10።
ስለዚህ ሚያዝያ 10 ስቅለት ይውላል ማለት ነው።
5. የትንሣኤ ተውሳክ 9 ነው ። 9+3=12 ። ስለዚህ ሚያዝያ 12 ትንሣኤ ይውላል ማለት ነው።
6. የርክበ ካህናት ተውሳክ 3 ነው። 3+3=6። ስለዚህ ርክበ ካህናት ግንቦት 6 ይውላል ማለት ነው።
7. የዕርገት ተውሳክ 18 ነው። 18+3=21። ስለዚህ ዕርገት ግንቦት 21 ቀን ይውላል ማለት ነው።
8. የጰራቅሊጦስ ተውሳክ 28 ነው። 28+3=31። ስለዚህ ጰራቅሊጦስ ሰኔ 1ቀን ይውላል ማለት ነው።
9. የጾመ ሐዋርያት ተውሳክ 29 ነው።
29+3=32 በ30 ሲገደፍ =2 ። ስለዚህ
ጾመ ሐዋርያት ሰኔ 2 ይውላል ማለት ነው።
10. የጾመ ድኅነት ተውሳክ 1 ነው። 1+3=4። ስለዚህ ጾመ ድኅነት ሰኔ 4 ቀን ይገባል ማለት ነው።

❗ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድር❗

።።።። ።።።።
።።።።። ።።።።።
።።።።። ።።።።።

Alex.Com (. አለሙ በየነ. - Click Ethiopia )

ፔጁን የቅዱስ ላሊበላ ገፅዎች Face of St.Lalibela

Address

Lalibela

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Travel Ethiopia tips posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Travel Ethiopia tips:

Share

Category