Loza Lalibela Tours PLC

Loza Lalibela Tours PLC My name is Tadesse Tenaw. I was born in 1978 E.C. I am 10 years experience in the industry.

when i was 9 years old i started to attuned my primarily school and move on to high school
I graduated my BA degree at DBU and my MSC at woldia university.

30/07/2026
14/07/2026
11/07/2026

ከእንግዳ ሽልማት አንቀበልም!

"የላስታ አርበኞች፦ ''

"የላስታ ህዝብ ኩሩ ነው እንሰማ ነበር፤ሀቅ መሆኑን በአካል አረጋገጥን" ቀዳማዊ ኃ/ስላሴ(ጃንሆይ)

የሆነው እንደዚህ ነው።

ጃንሆይ በ1928 ዓ.ም ከማይጨው ሲመለሱ ከመኳንንቶቻቸው ጋር በቅዱስ ላሊበላ አድርገው ወደ አ.አበባ በተመለሱበት ወቅት ሀገራቸው ድል ከቀናት የሚል ብፅዓት አስገብተው ነበር።

ስለሆነም፦በ1951 ዓ.ም በልዩ ትዕዛዝ፣አርሷደሮች መሬታቸውን በነፃ ለመስጠት ፍቃደኛ ሆነው፣የአውሮፕላን ማረፊያው ከተሰራ በኋላ በህዝብ ጉልበት የ23 ኪ.ሜ ጥርጊያ መንገድ ከተሰራ በኋላ፡ጃንሆይ ወደ ቅዱስ ላሊበላ መጥተው የግብርማብላት ስነ-ስርዓት ከተከናወነ በኋላ በህዝቡ ዘንድ በታሪክ ከፍተኛ እና ደማቅ ዝግጅት ተደረገ።በዚህ ዝግጅትም አዝማሪው ስለ 5(አምስት) ዓመቱ ፀረ-ቅኝ ገዥ ተጋድሎ እየተገጠመ ይሸለላል።የላስቴይቱ ልጅ

አርበኛው፣በጃርጉና፣በስገልዳ፣በተከዜ ጥላትን ሲያደባዬው እየተባለ ይገጠማል።ታዳ የላስታ አርበኞች፦የእነ ደጃዝማች ወንደወሰን ካሳ፣በእነ ደጃዝማች ሀይሉ ከበደ፣ደጃዝማች ወርቅነህ፣ደጃዝማች አባተ በዛ፣ፊታወራሪ ሀይሉ ክብረት፣የእነ ፊታወራሪ ድህኒ ዘገየ፣በእነ ግራዝማች አባይ ይማኑ እየተመሩ በአምስት ዓመቱ ጦርነት ላይ የፈፀሙትን ጀግንነት እሳቸው በስዴት ሆነውም በጥላት ልሳን ሳይቀር የሰሙት

ንጉሰ ነገስቱ ፤በወቅቱ ለነበሩ ፕሮግራም አዘጋጆች ጀግንነት ለፈፀሙ እና በበጎ ስራ ለሚታወቁ ሰዎች ሽልማት መስጠት ስለምፈልግ መዝግባችሁ አምጡልኝ በተባሉት መሰረት አዘጋጆቹ በተሰጣቸው ትዕዛዝ መሰረት የላስታ አርበኞች በታዋቂ ተግባር

የሚታወቁ ሰዎችን ልትሸለሙ ነው፤ተመዝገቡ ተብላችኋል ሲሏቸው፥የአርበኞቹ መልስ እንዲህ የሚል ነበር። "እኛ ንጉሳችን አክብረውን በእንግድነት ስለመጡ፤ጨምረን እንንከባከባቸዋለን እንጅ ሽልማት አንቀበልም የሚል ነበር።"

ጃንሆይም በአንፃሩ አርበኞቹ ያን መልስ እንደመለሱ ሲነገራቸው፥ እንዲህ አሉ።

" የላስታ ህዝብ ኩሩ ነው ሲባል እንሰማ ነበር፤ይሄን በአካል አረጋገጥን አሉ" :-

ዜና፦ላሊበላ ነገደ ዛግዌ ስርወ-መንግስትና አብያተ መቅደሱ፤

በደጃች ብርሃነ መስቀል ደስታ የተፃፈ፤

ይሄን ፅሑፍ ድጋሜ ማጋራት ያስፈለገኝ..... የላስታ ህዝብ አይደለም ሊለምን የደም ዋጋ ለከፈለው ነገር እንኳን፣ሽልማት የማይፈልግ ጠንካራ ስነ-ልቦና ያለው ህዝብ መሆኑን ከታሪክ ጋር አጣቅሼ ለመግለፅ ነው።
✍️ @ኦርያ አማራ

Lalibela

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) Henoke Seyuome Hagere ተጓዡ ጋዜጠኛ /ሄኖክ ስዩም/ Visit Amhara Mengistu Gobezie

13/06/2026

አዝናኝ ጥያቄ፡
ጠዋት በአራት እግር፣ ቀትር ላይ በሁለት እግር፣ ማታ ደግሞ በሶስት እግር የሚጓዘው ምንድን ነው?

A) የሰው ልጅ
B) ድመት
C) ጦጣ
D) ውሻ

Address

Lalibela
Lalibela

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Loza Lalibela Tours PLC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category