18/01/2026
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በአማን ከተማ ለሚኖሩ አካል ጉዳተኛ ወገኖቻችን የዊልቼር ድጋፍ አደረጉ
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በዛሬው ዕለት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ቤንች ሼካ ዞን፣ በሚዛን አማን ከተማ ለሚኖሩ አካል ጉዳተኛ ወገኖቻችን የዊልቼር ድጋፍ አድርገዋል።
በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የሚመራው የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት ሥራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለአካል ጉዳተኞች ልዩ ትኩረት በመስጠት የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ በርካታ ሥራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።
በዛሬው ዕለት የተደረገው ይህ ድጋፍ ልጆቻቸው የአካል ጉዳት ገጥሟቸው ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀስ ለተቸገሩ ወላጆችና ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው ለመማርም ሆነ ለመሥራት ለተቸገሩ ወገኖቻችን እገዛ የሚያደርግ ድጋፍ ነው።