Vacation on Bale mauntains national park and tour guide

Vacation on Bale mauntains national park and tour guide Create stable life and make happy our guests.

14/05/2026

ብሔራዊ ፓርኮችን በቴክኖሎጂ ለመጠበቅ የሚያስችል የሰለጠነ የሰው ኃይል እየተገነባ ነው፡- የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን**************ብሔራዊ ፓርኮችን በቴክኖሎጂ ለመጠበ...
14/05/2026

ብሔራዊ ፓርኮችን በቴክኖሎጂ ለመጠበቅ የሚያስችል የሰለጠነ የሰው ኃይል እየተገነባ ነው፡- የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን
**************

ብሔራዊ ፓርኮችን በቴክኖሎጂ ለመጠበቅ የሚያስችል የሰለጠነ የሰው ኃይል እየተገነባ መሆኑን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን ገለጸ።

በኢትዮጵያ የሚገኙ ብሔራዊ ፓርኮችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ጥበቃ እንዲያገኙ ለማድረግ፣ የሰለጠነ የሰው ኃይል የማፍራት ሥራ በስፋት እየተከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል።

የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ለሁለተኛ ዙር ለሦስት ወራት ያሰለጠናቸውን 44 የፓርክ ጥበቃ ባለሙያዎችን (ሬንጀሮችን) ዛሬ አስመርቋል።

ሰልጣኞቹ የአካል ብቃት ስልጠና ከመውሰዳቸው ባለፈ፣ እንደ ጂፒኤስ እና ኧርዝ ሬንጀር ያሉ ከሳተላይት ጋር የተገናኙ ዘመናዊ መሣሪያዎችን በመጠቀም መረጃዎችን የመከታተልና ወደ ማዕከል የማድረስ ብቃት አግኝተዋል።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንደገለጹት፤ ፓርኮችን በዋናነት የሚጠብቀው የአካባቢው ማኅበረሰብ ቢሆንም፣ ሕገወጥ ድርጊቶችን በብቃት ለመከላከል ቴክኖሎጂን መጠቀም የሚችል የሰለጠነ የሰው ኃይል አስፈላጊ ነው።

የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ኃላፊ አቶ ሻሚል ከድር በበኩላቸው፤ ባለፈው ዓመት ከሰለጠኑት 35 ባለሙያዎች ጋር ተዳምሮ አሁን ላይ የፓርኩ ጠባቂዎች ቁጥር 79 መድረሱን ጠቅሰው፣ ይህም የፓርኩን ጥበቃ በአስተማማኝ ሁኔታ ለማጠናከርና ሕግ ለማስከበር ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር አብራርተዋል።

በባዬ ሙላት

14/05/2026
17/10/2025
17/10/2025
10/07/2025
04/06/2025

Address

Bale Robe Dinsho Town
Robe

Telephone

+251919098844

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Vacation on Bale mauntains national park and tour guide posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Vacation on Bale mauntains national park and tour guide:

Share

Category