05/11/2026
ለበዓለ ዕርገት የንግሥ ጉዞ ወደ መንዝ እመጓ ቅዱስ ዑራኤል
✥ መነሻ ግንቦት 11
✥ መመለሻ ግንቦት 14
✥ ቦታው ላይ ምግብና ማረፊያ ቤትን ጨምሮ 4800 ብር
✥✞✥ ቅዱሳት መካናትን ለተዋህዶ ልጆች ሁሉ ማስተዋወቅ የሁላችንም ክርስቲያናዊ ግዴታ ነውና ጦማሩን አንብበው እርስዎ በሚጠቀሙባቸው ድረገጾች ላይ Share, Tag, Like, Comment & Forward... በማድረግ የቅዱሳት መካናቱን በረከት እንዲያገኙ ለተፈቀደላቸው ሁሉ የመባረካቸው ምክንያት ይሁኑ።
👉 {በእመጓ ላይ ጌታችን ለቅ/ዑራኤል፦ "አስቀድሜ በታላቁ ዐምደ ወርቅ ስሙን ያልጻፍኩትን ሰው ይህንን ደጅ አላስረግጠውም!" ብሎ የተገባለትን ቃል ልብ ይበሉ!!!
👉 እመጓ ( እመ እጓል) 👈
[ጌታችን፦ "አስቀድሜ በታላቁ ዐምደ ወርቅ ስሙን ያልጻፍኩትን ይህንን ደጅ አላስረግጠውም! ይህንን ደጅ የተሳለመ በግንባሩ ላይ «ቅዱስ ዑራኤል» የሚል ስውር ጽሑፍ በወርቅ ቀለም ይጻፍበታል፤ ባረፈ ጊዜም ዋስ ጠበቃ ሆኖት ባሕረ እሳትን ይሻገራል ወቀሳ ከሰሣም አይኖርበትም።" ብሎ ለቅዱስ ዑራኤል ቦታውን ባርኮ አስራት አድርጎ ሲሰጠው ቃል የገባበት፣
✝️ ለሊቀ ሰማእታት ቅዱስ ጊዮርጊስና ለጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ኢትዮጵያን አስራት አድርጎ የሰጠበት፣
✝️ እመቤታችን በስደቷ ጊዜ በኪደተ እግሯ የባረከቺውና ልጇ ወዳጇም፦ ይህንን ቅዱስ ቦታሽን "እስከ ዳግም ምጽዓቴ ድረስ 6000 እሳታዊያን መላእክት ይጠብቁልሻል።" ብሎ ቃልኪዳን የሰጠበት፣
✝️ የአረመኔዋ ዮዲት ጉዲት ጦር በጥበበ እግዚአብሔር የተደመሰሰበት ደብረ መዊዕ፣
✝️ እልፍ አዕላፍ ቅዱሳን የተጋደሉበትና የሚጋደሉበት መካነ ሱባዔ ወአርምሞ፣
✝️ በርካታ ምስጢሮችን የያዘና ላደለውም የሚገለጥበት መካነ ኅቡዓን፣
✝️ ግማደ መስቀሉ ለ14 ቀናት የተቀመጠበት፣
✝️ ቅዱስ ዑራኤል በደመ ክርስቶስ ዓለምን የቀደሰበት የብርሃን ጽዋ የተቀመጠበት ድንቅ ቦታ፣
✝️ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ምስጢረ ቁርባንን ሲመሰርት በቅዱሳት መለኮታዊ እጆቹ የጨበጠው ጽዋ የሚገኝበት መካነ ቅርስ፣
✝️ ከአዳም ጀምሮ የተነሱ ነቢያትና የሌሎችም ቅዱሳን ቅዱስ ዐጽም ከመስቀሉ ጋር ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ ያረፈበት ቅዱስ ቦታ፣
✝️ መስቀሉን ይዘው የመጡ ቅዱሳን የባረኩት የቅዱሳን መካነ ጸሎት፤
✝️ ከዕለተ ዓርብ ስቅለት ጀምሮ እስካሁን ድረስ ወደፊትም ከዋክብት ዘወትር የሚረግፉበትና ይህንንም ብዙዎች በቦታው ላይ ሱባዔ የያዙና ኑዋሪዎቹ ማታ ማታ የሚያዩበትና ሕያው ምስክር ያለው ተአምረኛ ገዳም፣
✝️ "ጌታ በማቴ ፳፬ ላይ የተናገረው ቃል የሚፈጸምበትን፣ ወንድም በወንድሙ ላይ የሚከፋበትን ክፉውን ዘመን 8ኛውን ሺህ እንዳታሳይኝ ከልጅሽ አማልጅኝ?" ብሎ እጅግ የሚወዳትና የሚያገለግላትን እመቤታችንን በመለመን ፰ኛው ሺህ በመስከረም ከመግባቱ በፊት በወርኀ ነሐሴ ያረፈው ደጉ ንጉሥ አፄ ናዖድ ያሰራት ስዕለት ሰሚዋ ምስዓለ ማርያም (ቀጭን አምባ ማርያም) የምትገኝበት፣ ...ግሩም ገዳም ነው።
🎁 በጉዟችን የምንሳለማቸው ቅዱሳት መካናት፦
→ ዋሻ አቡነ ዘርዓ ብሩክ ገዳም፣
→ እመጓ ቅ/ዑራኤል፣
→ ጻድቃኔ ማርያም፣
→ ዘብር ቅዱስ ገብርኤል፣
→ ቀጭን አምባ ምስዓለ ማርያም፣
→ እመ እጓል ቅ/እግዚአብሔር አብ፣
→ እመቤታችን በስደቷ ጊዜ ያረፈችበትና በኪደተ እግሯ የባረከቺው የኅቡዓን በዓት ደብረ ክሊና (ገሊላ)፣
→ ቅ/ዑራኤል ደመ መለኮትን ለዓለም ሁሉ የረጨበት ብርሃናዊው ቅዱስ ጽዋ በክብር የተቀመጠበት እና ፲ሩ ቅዱሳን ቅዱስ መስቀሉን ወደ ግሸን ሲወስዱ ለ14 ቀናት ያሳረፉበት ምስጢራዊው ደብረ ቆጵሮስ፣... ወዘተ የምንሳለምበት ልዩ ጉዞ ነው።
* መነሻ፦ ግንቦት 11 ከጠዋቱ
→ 10:30 አራዳ ቅ/ጊዮርጊስ፣
→ 11:00 መገናኛ ማራቶን ሕንፃ
→ 11:30 ጣፎ አደባባይ
* መመለሻ ግንቦት 14 (ለ4 ቀናት)
✞❖✞ የቀሩን ወንበሮች ጥቂት ብቻ ናቸው፤ ይደውሉልና አብረውን ይጓዙ!!!
{አስቀድመው ድርሣነ ዑራኤልንና እመጓ መጽሐፍን ቢያነቡ ጥሩ ነው}
#ለምዝገባ (ትኬት ለመቁረጥ)፦
👉🏾 መኮሬታ የገዳማት ትሩፋት
👉🏽 አድራሻ፦ መገናኛ ማራቶን ሕንፃ 1ኛ ፎቅ 36 ቁጥር
👉🏽 ባላችሁበት አካባቢ በሚከተሉት መ/ር አንተነህ ውብሸት የባንክ አካውንቶች በማስገባት ደረሰኙን (Screenshot) በቴሌግራም መላክና በጉዞውም ቀን ይዞ መምጣት።
☞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000355477448
Swift Code: CBETETAA
☞ አቢሲኒያ ባንክ 73439825
Swift Code: ABISETAA
☞ አሐዱ ባንክ 0042939910101
☞ አማራ ባንክ 9900001752271
☞ አዋሽ ባንክ 01320104564900
☞ ቴሌ ብር 0901070707 / 0911289877
👉 ፦ የቀበሌ መታወቂያ (ፓስፖርት)፣ ለብርድ የሚሆን ወፍራም ጃኬት፣ ለእግር መንገድ የሚሆኑና ተቀያሪ ጫማዎች፣ ሌሊት የሚለበስ ስሊፒንግ ባግ / ወፍራም ጋቢ/ ወፍራም ወይባ/ ፎጣ/ ቀለል ያለ ብርድ ልብስ/፣ ክርስቲያናዊ አለባበስ፣ ጃንጥላ፣ የእጅ ባትሪ፣ ሰዓት አክባሪነት፣ ታጋሽነት፣ የወጡበትን መንፈሳዊ ዓለማ ለማሳካት በጋራ መትጋት...
★ በማኅበራችን የጉዞ መርሐ ግብራት መሳተፍ ከፈለጉ ሳያመነቱ ይደውሉልንና አብረን እንጓዝ!!! ለበለጠ መረጃ በሚከተሉት የስልክ አድራሻዎች በመደወል ፈጥነው ይመዝገቡ!
☞ 0901070707
☞ 0911289877
ማኅበረ ቅዱስ ፊልጶስ ወአቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ