09/05/2026
ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ለነበራቸው አስተዋፅኦ እውቅና ተሰጣቸው
ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በመሎ ኮዛ ወረዳ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተገዙ የመንገድ መሠረት ልማት ማሽነሪዎች ግዢ ለነበራቸው አስተዋፅኦ ላበረከቱት ድጋፍ እውቅና ተሰጣቸው
በጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ የመንገድ መሠረተ ልማት ጥያቄዎችን በራስ አቅም በመፍታት የአካባቢውን ዕድገትና ልማት ለማፋጠን በወረዳው አስተዳደርና ሕዝብ የጋራ ትብብር ከ344 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዙ 11 ማሽነሪዎች እና የእርሻ ትራክተሮች ምረቃና ቀጣይ የልማት ትብብር መርሃ ግብር በላሃ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
የክልሉ መንግስት በህብረተሰብ ተሳትፎ በተገዛው ማሽነሪ የ25 ሚሊዬን ብር ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም የግዢ ሂደቱ እንዲፋጠን በማድረግ እገዛ አድርጓል።
ክቡር ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በመሎ ኮዛ ወረዳ ላሃ ከተማ በተዘጋጀው የምረቃ መርሃ ግብር ለነበራቸው አስተዋፅኦ ላበረከቱት ድጋፍ እውቅና ሰጥቷቸዋል።