
26/06/2025
አረጋጊው መልዐክ
አረጋጊው መልአክ የመላእክትን ዓለም
ገብርኤል አንተ ነህ አብሳሪ ለማርያም
መተህ አረጋጋን ሰላምን ተናገር
እንጽና በእምነት እንኑር በፍቅር/2/
አዝ
ባለንበት እንቁም እንፅና በእምነት
እስከምናውቅ ድረስ የፍጥረቱን አባት
ብለህ ስትናገር ገብርኤል በአርያም
በቃልህ ጸንተዋል እስከ ለዘለዓለም
አዝ
የዱራውን ሜዳ ያንን የሞት መንደር
ከሰማያት ወርደህ ሞላኸው በመዝሙር
መጠፋፋት ይብቃ ይብዛ ሰላማችን
ገብርኤል አትለይ ቁም ከመኃላችን
አዝ
በገሊላ መንደር ተልከህ ከእግዚአብሔር
ደስታ ይገባሻል ውዳሴ እና ክብር
ብለህ በትህትና የምስራች አልካት
ለድንግል ማርያም ደስታን አበሰርካት
አዝ
ቂርቆስ ኢየሉጣ ለአምላክ ቢታመኑም
በሚፍለቀለቀው ቢጣሉ ከጋኑም
ገብርኤል ስትደርስ ውኃው ቀዘቀዘ
ሞትን ያሸንፋል ለአምላክ የታዘዘ
ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
💚 💚
💛 💛
❤️ ❤️